ሽሬ ታነባለች (Shire Reads)

shire 1.jpg

shire 2.jpg

shire3.jpg

shire4.jpg

shire 6.jpg

shire 8.jpg

shire 10.jpg

በየዓመቱ ጥሪ 7 በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ በድምቀት የሚከበረው በተለምዶ “ስላሴ ሽሬ” የሚባለውን ሃይማኖታዊ በዓል ምክንያት በማድረግ የንባብ ጊዜና የመፃህፍት እርዳታ ተካሄደ፡፡ባለፈው ዓመት በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች #ኩስምን-ንባብን በሚል በማህበራዊ ሚድያ የጀመሩት የንባብና የመፃህፍት እርዳታ እንቅስቃሴ በመደገፍ አክሱም ዩኒቨርሲቲ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ ሲሆን በአክሱም በህዳር ፅዮን በዓል የተካሄደው የተሳካ የመፃህፍት እርዳታ ማስተባበሩ ይታወሳል፡፡ሰሞኑን በሽሬ ከተማ በተካሄደው ዝግጅት ላይ አንድ ሺህ መፃህፍት ለከተማው የህዝብ ቤተ-መፃህፍትና በዞኑ በተለያዩ አከባቢዎች ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንደሚከፋፈል በዓሉን ካስተባበሩት ወጣቶች አንዱ የሆነው #HaHu ገልፆልናል፡፡

የንባብ ላይ ትኩረት አድርጎ ተዘጋጅቶ በነበረው አውደ ጥናት ላይ በርከት ያሉ ወጣቶች፣ ተማሪዎችና የእንቅስቃሴው ደጋፊዎች የተገኙ ሲሆን የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ፣ የቀድሞ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ምትኩ ሃይሌ እና የሼባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ መስራች የሆኑ መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡