በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ሎካል ሪሰርች (local research) ተካሄደ

R12.jpg

በአዉደ ጥናቱም 50 የምርምር ጽሁፎች በዩኒቨርሲቲዉ መምህራን የቀረበ ሲሆን የመምህራን የምርምር አቅም እና የእዉቀት ሸግግር እንደሚያሳድግ ተገልጻል፡፡የምርምር እና ድህር ምረቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሙልጌታ በሪሁ ጥናቶቹም ሀገሪቱ ያለችበትን ወቅታዊ ጉዳይ እና የትራንስፎርሜሽን እቅድ የሚያግዝ እንዲሁም ማህበረሰቡ ጋር ወርዶ የመስራት እና ችግሮቹን የመፍታት ሀላፊነት እንዳለባቸዉ ገልጸዋል፡፡ በአዉደ ጥናቱ ከተዳሰሱት የምርምር ጽሁፎች መካከል በጤና ቴክኖሎጂ ዉሃ አጠቃቀም እናቶች እና ህጻናት መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ይጠቀሳሉ፡፡የተመረጡ ጥናታዊ ጽህፎች ተጨማሪ ምርምር ተደረጎባቸዉ እና ከማህበረሰቡ ጋር ዉይይት ተካሂዶባቸዉ በጀቱ ተመድቦ ወደ ተግባር ዉለዉ ለማህበረሰቡ ጥቅም የሚሰጡበት መንገድ ይፈጠራል ተብላል በተጨማሪም ጽሁፎቹ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደዉ የምርምር አዉደ ጥናት የመሳተፍ እድል እንደሚያገኙ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡አዉደ ጥናቱ በዩኒቨርስቲዉ መካሄዱ በምርምሩ ዘርፍ የመምህራን ተሳትፎ ለማሳደግ እና አዳዲስ የምርምር ጽንሰ ሀሳቦች እንዲስፋፋ በር ከፋች ሲሆን የዩኒቨርሲተዉ ገጽታ ከማሳደግ አካያ  ትልቅ አስተዋጾ አለዉ ተብላል፡፡

 

  ሴቶች አለመሳተፋቸዉ እንደ ችግር የታየ ሲሆን ያልተሳተፉበትን ምክንያት በማጥናት በቀጣይ የሚሳተፉበት ሁኔታ እንደሚመቻች ተጠቁማል፡፡መድረኩ በየአመቱ ቀጣይነት እንደሚኖረዉ እና የተሳታፊ ቁጥር አነስተኛ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዉ መምህራን እና ተማሪዎች በአዉደ ጥናቶች ላይ የመሳተፍ ባህላቸዉን እንዲያሳድጉ ጠይቀዋል፡፡በአዉደ ጥናቱም 50 የምርምር ጽሁፎች በዩኒቨርሲቲዉ መምህራን የቀረበ ሲሆን የመምህራን የምርምር አቅም እና የእዉቀት ሸግግር እንደሚያሳድግ ተገልጻል፡፡የምርምር እና ድህር ምረቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሙልጌታ በሪሁ ጥናቶቹም ሀገሪቱ ያለችበትን ወቅታዊ ጉዳይ እና የትራንስፎርሜሽን እቅድ የሚያግዝ እንዲሁም ማህበረሰቡ ጋር ወርዶ የመስራት እና ችግሮቹን የመፍታት ሀላፊነት እንዳለባቸዉ ገልጸዋል፡፡

በአዉደ ጥናቱ ከተዳሰሱት የምርምር ጽሁፎች መካከል በጤና ቴክኖሎጂ ዉሃ አጠቃቀም እናቶች እና ህጻናት መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ይጠቀሳሉ፡፡ የተመረጡ ጥናታዊ ጽህፎች ተጨማሪ ምርምር ተደረጎባቸዉ እና ከማህበረሰቡ ጋር ዉይይት ተካሂዶባቸዉ በጀቱ ተመድቦ ወደ ተግባር ዉለዉ ለማህበረሰቡ ጥቅም የሚሰጡበት መንገድ ይፈጠራል ተብላል በተጨማሪም ጽሁፎቹ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደዉ የምርምር አዉደ ጥናት የመሳተፍ እድል እንደሚያገኙ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡አዉደ ጥናቱ በዩኒቨርስቲዉ መካሄዱ በምርምሩ ዘርፍ የመምህራን ተሳትፎ ለማሳደግ እና አዳዲስ የምርምር ጽንሰ ሀሳቦች እንዲስፋፋ በር ከፋች ሲሆን የዩኒቨርሲተዉ ገጽታ ከማሳደግ አካያ  ትልቅ አስተዋጾ አለዉ ተብላል፡፡ሴቶች አለመሳተፋቸዉ እንደ ችግር የታየ ሲሆን ያልተሳተፉበትን ምክንያት በማጥናት በቀጣይ የሚሳተፉበት ሁኔታ እንደሚመቻች ተጠቁማል፡፡መድረኩ በየአመቱ ቀጣይነት እንደሚኖረዉ እና የተሳታፊ ቁጥር አነስተኛ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዉ መምህራን እና ተማሪዎች በአዉደ ጥናቶች ላይ የመሳተፍ ባህላቸዉን እንዲያሳድጉ ጠይቀዋል፡፡