ፕሮፌሰር ኢፍሬም ይሳቅ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ጎበኙ

Prof12_2.jpg

ፕሮፌስሩ በጉብኝት ወቅት ለዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ ባሰሙት ንግግር ኢትዮጵያ የመላው አፍርካውያንና የጥቁር ህዝቦች የታሪክና የኩራት መባቻ መሆኑዋን ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአለም ደረጃ የታወቀ የራስዋ ፊደልና ፅሑፍ ካሉዋላት አገራት የምትመደብ እና በጣም የምያኮራ ባህልና ታሪክ ያላት ሃገር እንደሆነች በመጠቆም፣ ያለንን አኩር ታሪካችንን እና እሴቶቻችን በማወቅ ረገድ ገና ብዙ የሚቀረን ነገር አለ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ኢፍሬም ይሳቅ በንግግራቸው ወቅት፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ፕሮፌሰሩ እንዳሉት ከሆነ ኢትዮጵያ ከተወሰኑ አመታት በፊት በራብና በድንቁርና ስትታወቅ እንደነበረችና ያሉዎት መልካም ባህሎችና እሴቶቻችን ተደብቆው እንደነበሩ ገልፀው፣ አሁን ግን ያ መጥፎ ታሪካችን ተደምስሶ ኢትዮጵያ የቡዙ ታሪክና ስልጣኔ ቀዳምት ከሚባሉ ብሎም በፈጣን እድገት መንገድ ከሚገኙ አገራት አንድ ናት፡፡

ፕሮፌሰሩ በንግግራቸው ወቅት አክለውም ኢትዮጵያ ለመላዊ የአፍሪካ አገራት የሰላምና ነፃነት ተምሳሌት በመሆን አፍርካዊያን ከባርነት እንዲላቀቁ እና ለነፃነታቸው እንድዋጉ ትልቅ ተምሳሌት በመሆን የራስዋንምና የተዋጣች አገር ናት ነው ያሉት፡፡

ለዚህ ማሳያ ደሞ የኢትዮጵያ ንጉስ እንደ አምላክ የምታይበት የጥቁር ህዝቦች አገሮች እንዳሉም ነው ፕሮፌሰሩ በንግግራቸው ወቅት የጠቀሙት፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በአለም ደረጃ መፅሃፍ ቅዱስ ከተተረገምባቸው ሰባት /7/ ቋንቋዎች የአክሱም የግእዝ ቋንቋ አንድ መሆኑን ጠቁሞው፡፡ በታሪክና በሃይማኖት ጥናት ማድረግ የሚፈልግ ሁሉ የግእዝ ቋንቋ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ማወቅ አለበት ነው ያሉት ለዚህ ሁሉ ታሪክ ደግሞ አክሱም መሰረት ናት ነው ያሉት፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቅርብ ግዚያት ጀምሮ በአገራችን አንድ አንድ አከባቢዎች እየተስተዋሉ ያሉ የሰላም ማጣት እና አለመረጋጋት እንደሚያሳስባቸው በመግለፅ ኢትዮጵያዊያን የባህልና ቋንቋ ልዩነቶች ውበታችን መሆናቸው አውቀን ድሮ የነበረን አንድነትና መልካም ባህላችን አብረን ተባብረን ልንጠብቃቸው ይገባናል ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ፡፡

ሰላም ከሌለ እድገት አይኖርም ያሉት ፕሮፌሰር ኢፍሬም ሰላማችን ጠብቀን በታሪካችን ኮርተን በአብሮነት እና በመከባበር ልንኖር ይገባናል፤ ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ የተሳሰረ ህዝብ በመሆኑ ከማንም ግዜ በላይ ያደርገዋል ብለው እንዲያምኑም ገልፀዋል፡፡

ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ በ Harvard University የ Afro-American studies መስራች እና የመጀመሪያ ፕሮፌሰር ሲሆኑ ዘርፍ ብዙ ምሁር ናቸው፡፡ ፕሬፌሰሩ ወደ 17 ያህል ቋንቋዎች የሚናገሩ እና አሜሪካን አገር ጨምሮ በተለያዩ አገሮች በማስተማር ትልቅ ልምድ ያካበቱ ከመሆናቸውም በተጨማሪ በኢትዮጵያና በኤርትራ ብሎም ለመላዊ አለም ሰላም እንዲኖር የሰላም ኢንስትትዩት በመክፈት ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረጉ ካሉ ብርቅየ የኢትዮጵያ ሙሁራን ግንባር ቀደም ናቸው፡፡        

ፕሮፌስሩ በጉብኝት ወቅት ለዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ ባሰሙት ንግግር ኢትዮጵያ የመላው አፍርካውያንና የጥቁር ህዝቦች የታሪክና የኩራት መባቻ መሆኑዋን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአለም ደረጃ የታወቀ የራስዋ ፊደልና ፅሑፍ ካሉዋላት አገራት የምትመደብ እና በጣም የምያኮራ ባህልና ታሪክ ያላት ሃገር እንደሆነች በመጠቆም፣ ያለንን አኩር ታሪካችንን እና እሴቶቻችን በማወቅ ረገድ ገና ብዙ የሚቀረን ነገር አለ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ኢፍሬም ይሳቅ በንግግራቸው ወቅት፡፡