አክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ለመከላከል በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ አስታወቀ

አክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ለመከላከል በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ አስታወቀ
ዩኒቨርሲቲው ከእጅ ንክኪ ነፃ 80 የእጅ መታጠብያና 1200 ሊትር ሳኒታይዘር የህዝብ አገልግሎት ለሚሰጥባቸው ተቋማት በስጦታ አበርክተዋል።
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ባለሞያዎች የተሰራው ከእጅ ንክኪ ነፃ የእጅ መታጠብያ እንዲሁም የተገዛው ሳኒታይዘር በማእከላዊ፣ ሰሜናዊ ምዕራብና ምዕራብ ትግራይ ለሚገኙ ህዝብ የሚገለገልባቸው ተቋማት እያከፋፈለ ይገኛል።
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን የኳራንታይን፣ ለይቶ ማቆያ፣ ማገገሚያና የምርመራ ማእከላት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ ገልፀዋል።


ዶ/ር ኪሮስ ህብረተሰቡ በሚገለገልባቸው ተቋማት የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነታቸው ለመቀነስ ያለመ የእጅ መታጠብያና የሳኒታይዘር ድጋፍ ማድረጋቸው አስታውቀዋል።
የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር መርሃዊ አብርሃ በበኩላቸው በኮሮና ቫይረስ የመከላከል ዘዴዎች ዙርያ የማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እየተሰጠ ነው ብለዋል።
ዶ/ር መርሃዊ አክለውም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ባለሞያዎች ለሶስት ቀናት የሚቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃግብር ለቫይረሱ በማያጋልጥ አኳሃን በማእከላዊ፣ ሰሜናዊ ምዕራብና ምዕራብ ዞኖች እንደሚሳለጥ አስታውቀዋል።
የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ በዚህ ፈታኝ ወቅት ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ለሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል።
አክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ለከባድ ማሕበረ-ኢኮነሚያዊ ተፅእኖ ስለሚዳርግ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል።

  

Written by