አክሱም ዩኒቨርሲቲ በቀን 1080 ናሙና መመርመር የሚችል የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ማእከል ተቋቋመ

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በቀን 1080 ናሙና መመርመር የሚችል የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ማእከል አቋቋመ

ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ዉጭ በሳይንስ ሙዝየም ከሚገኘው ግዝያዊ የህክምና ማእከል ናሙና በመዉሰድ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የሚካሄድበት ማእከል ግንባታዉ ተጠናቅቆ ምርመራ ተጀምረዋል፡፡

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ፣ ቅድስት ማርያም ሆስፒታል፣ የትግራይ የጤና ምርምር ኢንስቲትዩትና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመተባበር የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መጀመሩን የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ኃላፊ ዶ/ር ደጀን ገብረገርግስ ተናግረዋል፡፡

  

የምርመራ ማእከሉ መሳርያዎች ከቅድስት ማርያም ሆስፒታል እንዲሁም የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ግብርናና የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጆች በማሰባሰብ ተተክለዋል፡፡

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ማእከል በሁለት ሰዓት የ90 ናሙናዎች የምርመራ ዉጤት የሚሰጥ ሲሆን በቀን የ1080 ናሙናዎች ዉጤት ይሰጣል፡፡

ማእከሉ ለኮሮና ቫይረስ የምርመራ ሂደት በሚመጥን መልኩ በአዲስ ዲዛይን በአንድ ሳምንት ዉስጥ ግንባታው እንደተጠናቀቀ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕረዚዳንት ዶ/ር መርሃዊ ኣብርሃ ገልፀዋል፡፡

ማእከሉ በቀጣይነት የሞሎኪዩላር ላብራቶሪ የምርምር ማእከል ሆኖ እንደሚያገለግልም ዶ/ር መርሃዊ አክለዋል፡፡

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ማእከል በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የብቃት ማረጋገጫ ተለክቶ ብቁ ሆኖ መገኘቱን የትግራይ የጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ተወልደ ዉብኣየሁ ተናግረዋል፡፡

Written by