አክሱም ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ከ1.3 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት ለምግብነት የሚዉል ግብአት ድጋፍ አደረገ

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ከ1.3 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት ለምግብነት የሚዉል ግብአት ድጋፍ አደረገ

ዩኒቨርሲቲዉ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተወሰደ ባለዉ እርምጃ ምክንያት ኢኮነሚያዊና ማህበራዊ ቀዉስ እንዳይፈጠር እየተደረገ ላለዉ ጥረት ለመደገፍ በ1 ሚልዮን 353 ሺ 680 ብር የተገዛ 225 ኩንታል የተፈጨ ጤፍ፣ 60 ኩንታል ሩዝ፣ 60 ኩንታል በርበሬ፣ እንዲሁም 20 ኩንታል ሽሮ በማእከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብና ምዕራብ ትግራይ ለሚገኙ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በየዞኖቹ መስተዳደር እንዲከፋፈል ወስኗል፡፡

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በዚህ ፈታኝ ወቅት ከህብረተሰቡ ጎን በመቆም ማህበራዊ ኃላፊነቱ እንደሚወጣም አስታዉቋል፡፡

Written by