ማስታወቂያ ለቅድመ-ምረቃ መደበኛ ተመራቂ ተማሪዎችና የአራተኛ አመት የህክምና (C-II) ተማሪዎች

ማስታወቂያ ለቅድመ-ምረቃ መደበኛ ተመራቂ ተማሪዎችና የአራተኛ አመት የህክምና (C-II) ተማሪዎች
አክሱም ዩኒቨርሲቲ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል አስፈላጊ ቅድመ-ዝግጅት አድርጓል።
በመሆኑም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች እንዲሁም የአራተኛ አመት የህክምና ተማሪዎች (C-II) ከጥቅምት 26 እስከ 27 2013 ዓ.ም በየግቢያችሁ በመገኘት ተመዝግባችሁ ትምህርት እንድትጀምሩ እንገልፃለን።
ራሳችሁን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚያስፈልጉዋችሁ ቁሳቁስ በመያዝ በጉዞአችሁ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሚያደርጉዋችሁ ሁነቶች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እንመክራለን።
ማሳሰብያ
የተሰጠው የትምህርት ክፍለ ጊዜ አጭር በመሆኑ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆናችን እናሳውቃለን።

Written by